Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የምሥራቅ አፍሪካ አርብቶ አደሮች ኤክስፖ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የምሥራቅ አፍሪካ አርብቶ አደሮች ኤክስፖ በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ነው።

ኤክስፖው “አርብቶ አደርነት የምሥራቅ አፍሪካ ኅብረ – ቀለም” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በኤክስፖው የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ የመስኖና እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አይሻ መሃመድ (ኢ/ር) እና የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት አርብቶ አደር ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡

በተጨማሪም በኢትዮጵያ አርብቶ አደሮች የሚገኙባቸው ሰባት ክልሎች፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና አጋር ድርጅቶች ተሳትፈዋል፡፡

በይስማው አደራው

Exit mobile version