ቢዝነስ

የምርት ጥራት ደረጃ አላሟሉም በተባሉ 92 ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ

By Mikias Ayele

January 25, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የምርት ጥራት ደረጃ ባላሟሉ 92 ድርጅቶች ላይ የእርምት እርምጃ ወስጃለሁ አለ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፡፡

በ282 ድርጅቶች ላይ የምርት ጥራት ቁጥጥር ሥራ ተከናውኖ 60ዎቹ የጥራት ደረጃ ማሟላታቸው ተገልጿል፡፡

እንዲሁም 130 ድርጅቶች  ማስተካከያ አድርገው የተቀመጠውን መስፈርት እንዲያሟሉ መደረጉም ተጠቅሷል፡፡

92 ድርጅቶች ደግሞ የተቀመጠውን የጥራት ደረጃ ያላሟሉና ከደረጃ በታች በመሆናቸው እርምጃ መወሰዱን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ማኅበረሰቡም የሚሸምተውን ምርት ጥራት በማረጋገጥ ጤንነቱን መጠበቅ እንደሚገባው ሚኒስቴሩ አስገንዝቧል፡፡