አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኢትዮጵያ ዓየር መንገድ አገልግሎት በሳፈሪኮም ኤም ፔሳ የክፍያ አማራጭ በኩል ደንበኞች ክፍያ መፈፀም የሚችሉበት አዲስ አማራጭ ይፋ ሆኗል፡፡
አዲሱን የክፍያ አማራጭ ያስተዋወቁት የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ እና ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ናቸው፡፡
የክፍያ አማራጩም በኢትዮጵያ ዓየር መንገድ በኩል የሚጓዙ ደንበኞች የሳፋሪኮም ኤም ፔሳ የክፍያ አማራጭን ተጠቅመው ካሉበት ቦታ ክፍያ መፈፀም የሚችሉበት ነው ተብሏል፡፡
በቤተልሔም መኳንንት