Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሞሮኮ በአሰልጣኝ ዋሊድ ረግራጊ የሁለት ጨዋታዎች ቅጣት ይግባኝ ጠየቀች

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሞሮኮ በአሰልጣኝ ዋሊድ ረግራጊ የሁለት ጨዋታዎች ቅጣት ውሳኔ ላይ ለካፍ የይግባኝ ደብዳቤ ማስገባቷን የሀገሪቱ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታውቋል፡፡

አሰልጣኝ ዋሊድ ረግራጊ  አቻ በተጠናቀቀው የሞሮኮ እና ኮንጎ ጨዋታ በኮንጎ ብሄራዊ ቡድን አምበል ቻንሴል ምቤምባ ላይ በፈፀሙት ያልተገባ ባህሪ በካፍ የሁለት ጨዋታዎች እገዳ ተጥሎበት መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡

ካፍ የቅጣቱን ምክንያት በግልፅ ባያሳውቅም አሰልጣኝ ዋሊድ ረግራጊ በቻንሴል ምቤምባ ላይ የዘረኝነት ጥቃት በመሰዘራቸው መሆኑን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡

የአሰልጣኙን የዲስፕሊን ግድፈት ካጣራ በኋላ ካፍ  የሁለት ጨዋታ ቅጣት ያስተላለፈበት ሲሆን÷ውሳኔውን ተከትሎም የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለካፍ ይግባኝ መጠየቁ ተገልጿል፡፡

የቅጣት ውሳኔውን ተከትሎም አሰልጠኙ ትላንት ምሽት ሞሮኮ ዛምቢያን 1 ለ 0 ባሸነፈችበት ጨዋታ ላይ ያልተገኙ ሲሆን÷በቀጣይ በጥሎ ማለፉ በሚደረገው ሌላ አንድ ጨዋታ ላይም የማይገኙ ይሆናል፡፡

Exit mobile version