Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

8ኛው ከተማ አቀፍ የንባብ ባህል ፌስቲቫል መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ስምንተኛው ከተማ አቀፍ የንባብ ባህል ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ሙዚዬም መካሄድ ጀምሯል፡፡

የንባብ ፌስቲቫሉ “አንባቢ ትውልድ ለሀገር ብልፅግና” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በአዲስ አበባ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የባህል ዘርፍ ም/ሃላፊ አስፋው ኩማ÷የንባብ ፌስቲቫሉ በመዲናዋ ያለውን የንባብ ባሕል ለማዳበር ሚናው ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የከተማዋ ወጣቶች የንባብ ባህላቸው እንዲያድግ በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

በቢሮው የቱሪዝም ዘርፍ ም/ሃላፊ ሃፍታይ ገ/ እግዚአብሔር በበኩላቸው÷ከድህነትና ኋላ ቀርነት ለመላቀቅ ንባብ ትልቁን ድርሻ እንደሚወስድ ተናግረዋል።

ፌስቲቫሉ ለተከታታይ አምስት ቀናት እንደሚቆይ ተመላክቷል፡፡

በመለሰ ምትኩ

Exit mobile version