Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢራንና ቱርክ የእስራኤልና ሃማስ ጦርነት እንዲቆም ለማድረግ በጋራ እንደሚሰሩ ገለጹ

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢራንና ቱርክ የእስራኤል እና ሃማስ ጦርነት ወደ ቀጣናው እንዳይስፋፋ ለማድረግ በትብብር እንደሚሰሩ አስታውቀዋል፡፡

የኢራን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ ከቱርኩ አቻቸው ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን ጋር የእስራኤል እና ሃማስ ጦርነትን በተመለከተ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ሁለቱ መሪዎች በጋዛ የሚስተዋለውን ሰብዓዊ ቀውስ ለማስቆም እና ቀጣናዊ መረጋጋት እንዲኖር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መክረዋል፡፡

የእስራኤል እና ሃማስ ጦርነት የመካከለኛው ምስራቅ ቀጣናን ውጥረት ውስጥ እየከተተ መሆኑን በመጥቀስ÷ ጦርነቱ ወደ ቀጣናው እንዳይሰፋፋ መከላከል አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ለዚህም ሀገራቱ ድንበር ዘለል ግጭቶችን ለመከላከል በቅንጅት እንደሚሰሩ መስማማታቸው ነው የተገለጸው፡፡

ፕሬዚዳንት ራይሲ ወደ ቱርክ አንካራ ሲያመሩ ከፈረንጆቹ 2021 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ዓረብ ኒውስ በዘገባው አመልክቷል፡፡

የእስራኤል እና ሃማስ ጦርነት ያስከተለው ቀጣናዊ ውጥረት ለፕሬዚዳንቱ አስቸኳይ ጉብኝት ምክንያት ነው ተብሏል፡፡

Exit mobile version