Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አምባሳደር ምሥጋኑ ከአውሮፓ ኅብረት የሰብዓዊ መብቶች ልዩ ተወካይ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምሥጋኑ አርጋ ከአውሮፓ ኅብረት የሰብዓዊ መብቶች ልዩ ተወካይ ኢሞን ጊልሞር ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በተለያዩ ሀገራዊ፣ አኅጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች መክረዋል፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰቱ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ዓላማ አድርጎ እየተዘጋጀ ስላለው የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አምባሳደር ምሥጋኑ አብራርተዋል፡፡

በዚሁ መሠረት ፖሊሲው በመጠናቀቅ ላይ አፈጻጸሙም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ማስረዳታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲው ተጠያቂነትን እና ሰላምን ለማስፈን እንዲሁም አጠቃላይ የቀጣናውን ፀጥታ ማሳደግ ላይ ያተኮረ ስለመሆኑም አስረድተዋል፡፡

ኢሞን ጊልሞር በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ከሰሜኑ ግጭት ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ያሳየችውን ቁርጠኝነት አድንቀዋል፡፡

የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ መተግበር አስፈላጊ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

Exit mobile version