አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የገላጭ ጽሑፍና የኢትዮጵያን አስገዳጅ ደረጃ ሳያሟሉ እንዲሁም ደኅንነታቸውና ጥራታቸው ሳይረጋገጥ ገበያ ላይ የዋሉ 83 ምርቶችን ኽብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው አሳስቧል፡፡
44 ዓይነት የምግብ ዘይት ምርት እና 39 ዓይነት በአዮዲን የበለፀገ የምግብ ጨው ምርት ደኅንነታቸውና ጥራታቸው ያልተረጋገጡ መሆናቸውን ባለስልጣኑ በገበያ ቅኝት ሥራ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡
በተጨማሪም የሀገሪቱን አስገዳጅ ደረጃ እና የገላጭ ጽሑፍ ደረጃ ሳያሟሉና ሳይለጥፉ መገኘታቸው ተገልጿል፡፡
በመሆኑም ከታች በምስልና በስም የተጠቀሱት ምርቶች ደኅንነታቸውና ጥራታቸው ያልተረጋገጡና የሀገሪቱን አስገዳጅ ደረጃ የማያሟሉ በመሆናቸው ሕብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡
በዚህም አስገዳጅ የሀገሪቱን ደረጃና የገላጭ ጽሁፍ ደረጃን ሳያሟሉ ገበያ ላይ የተገኙ የምግብ ዘይት ምርቶች፡-
ሰመር ንፁህ የምግብ ዘይት፣ ማሚ የተጣራንፁህ የምግብ ዘይት፣ እስካይ /Sky Sun flower oil፣ ሳኒ /SANI Edible Cooking Oil)፣አዚማር/Azimar Sunflower Oil፣ኑራ ንፁህ የምግብ ዘይት፣ አበባ ንፁህ የምግብ፣ ዘይት፣አደይ ንፁህ የምግብ ዘይት፣ዘቢብ/Zebib Sunflower oil፣አስሊ ንፁህ የምግብ ዘይት፣ ሪል (Real Pure Food Oil)፣ዙፋን ንፁህ የምግብ ዘይት፣ ሀኒ(Hani Sunflower Oil)፣ዲና ንፁህ የምግብ ዘይት
ሊና ንፁህ የምግብ ዘይት፣ማማ የተጣራ የምግብ ዘይት፣አል ኑር Al-Nur Sunflowor Oil፣ዋሪዳ Warida sunflower Oil፣ዜድ ንፁህ የምግብ ዘይት፣ደሴት ንፁህ የምግብ ዘይት፣ከፍታ ንፁህ የምግብ ዘይት Pure Food Oil፣ንግስት ንፁህ የምግብ ዘይት Nigist pure Food oil፣ሸገር Sheger pure Edible Oil፣አሪፍ Arif የኑግ የምግብ ዘይት ፣አመለ AMEL Edible Oil
ብሉ የኑግ ዘይት፣ንፁህ Nitsuh Food Oil፣ ኡማ ንፁህ የምግብ ዘይት ፣ማዕድ Maed ንፁህ የምግብ ዘይት፣ ሀያት የተጣራ የምግብ ዘይት ፣የምስራች ንፁህ የምግብ ዘይት፣ ህብረት ንፁህ የምግብ ዘይት፣ጎንደር የምግብ ዘይት Gonder Food Oil፣ ዜማ Zema pure Edible Oil ፣ፋና fana ፣ናና የኑግና የለውዝ የምግብ ዘይት፣ሪም ንፁህ የምግብ ዘይት
አንድነት ANDNET፣ሲያም ንፁህ የምግብ ዘይት፣ቤላ የምግብ ዘይት፣ሐሊማ የምግብ ዘይት፣ወሲላ ንፁህ የምግብ ዘይት Wesila፣ዝና ንጹህ የምግብ ዘይት፣ሰነዓ ንጹህ የምግብ ዘይት ናቸው፡፡
አስገዳጅ የሀገሪቱን ደረጃና የገላጭ ጽሁፍ ደረጃን ሳያሟሉ ገበያ ላይ የተገኙ የምግብ ጨው ደግሞ፡-
አርኪ የገበታ ጨው ARKY IODIZED SALT፣ኢኮ አዮዳይዝድ ጨው EKKO IODIZED SALT፣ስጦታ ጨው SITOTA Iodized Salt፣መስቱራ ባለ አዮዲን የተፈጨ ጨው MESTURA REFIND & IODIZED SALT፣ አስቤዛ የገበታ ጨው Asbeza Iodized salt፣ዘሀራ የገበታ ጨው ZAHARA IODIZED SALT፣መነስ ጨው MENES IODIZED SALT፣ግዩን አዮዲን ጨው Ghion Iodin Salt
አርዲ የገበታ ጨው ARDI IODIZED SALT፣ሳሊህ የገበታ ጨው SLIHA IODIZED SALT፣ናና ጨው NANA SALT፣ቤስት የገበታ ጨው Best Iodized Salt፣ቅመም የገበታ ጨው Iodized Salt፣ረሃ የገበታ ጨው REHA IODIZED SALT፣አርዲ የገበታ ጨው ARDY IODIZED SALT፣አፊአ የገበታ ጨው AFIA IODIZED SALT፣ፋና የገበታ ጨው Fana table salt
እቴቴ የገበታ ጨው Etete Iodized Table Salt፣ልዩ ጣዕም የገበታ ጨው LIYU TAEM IODIZED Salt፣ሀሮኒ HARONI Table Salt፣ሮም ROME ንጹሁ የገበታ ጨው፣ቶፕ የገበታ ጨው TOP IODIZED SALT፣ጤና ጨው Tena Iodized salt፣ማሬ የገበታ ጨው MARE IODIZED SALT፣ሳፊ የገበታ ጨው SAFI IODIZED SALT
እሜቴ አዮዳይዝድ የገበታ ጨው Iodized Table Salt፣ሀላል የገበታ ጨው HALAL IODIZED SALT፣ጡልት ጨው TULIT SALT፣ሪል የገበታ ጨው REAL IODIZED SALT፣ጎልድ GOLD IODIZED SALT፣ስፔሻል የገበታ ጨው SPECIAL Iodized Table Salt፣ሰላም የገበታ ጨው IODIZED SALT፣ሸሙ በአዮዲን የበለጸገ የገበታ ጨው SHEMU IODIZED SALT
ኢምሬት ጨው Emirate salt፣ኑር NUR IODIZED SALT፣ሀገሬ አዮዳይዝድ ጨው HAGERE Iodized Salt፣ኢቲ ኤምኢየገበታ ጨው ET ME IODIZED SALT፣ማራኪ MARAKI በአዮዲን የበለጸገ የገበታ ጨው፣ታሪክ የገበታ ጨው TARIK TABLE SALT ናቸው፡፡
ሕብረተሰቡ ምርቶችን ከመግዛቱ በፊት የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃ ምልክት የለጠፉ መሆናቸውንና የምርት ገላጭ ጽሑፍ መኖሩን ማረጋገጥ እንደሚጠበቅበት ባለስልጣኑ አስገንዝቧል፡፡