Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አሜሪካ እና ብሪታኒያ በየመን ሁቲዎች ላይ ተጨማሪ ጥቃት ሠነዘሩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ እና ብሪታኒያ በየመን የሁቲ ኢላማዎች ላይ አዲስ ተከታታይ የዓየር ድብደባ መፈፀማቸው ተሰምቷል፡፡
 
የመሬት ውስጥ የመሳሪያ ግምጃ ቤት፣ የሁቲ ሚሳኤል እና የመቆጣጠሪያ ቦታን ጨምሮ ስምንት ኢላማዎች ላይ ጥቃት ማድረሱን የአሜሪካ መከላከያ ኃይል (ፔንታጎን) አስታውቋል፡፡
 
ፔንታጎን በይፋ ባቀረበው የጋራ መግለጫም በሁቲዎች ላይ ተጨማሪ ዙር ተመጣጣኝ እና አስፈላጊ ጥቃት መሰንዘሩን አረጋግጧል።
 
እርምጃው የተወሰደበት ዓላማም በቀይ ባሕር የነገሰውን ውጥረት ለማርገብ እና የቃጣናውን መረጋጋት ወደ ነበረበት ለመመለስ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡
 
አሜሪካና ብሪታኒያ ከፈረንጆቹ ጥር 11 በኋላ የጋራ ጥቃት ሲፈፅሙ ይህ ሁለተኛ ጊዜያቸው ሲሆን÷ አሜሪካ ግን በየመን የሁቲ ዒላማዎች ላይ ጥቃት ስታደርስ ለስምንተኛ ጊዜ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
 
ጥቃቱ የተካሄደውም ከአውስትራሊያ፣ ባሕሬን፣ ካናዳ እና ኔዘርላንድስ በተገኘ ድጋፍ መሆኑን የጋራ መግለጫው ማስታወቁን ቢቢሲ ዘግቧል።
 
ሁቲዎች “ከእስራኤል እና ከምዕራቡ ዓለም ጋር ግንኙነት አላቸው” በሚሏቸው በቀይ ባሕር የሚተላለፉ የንግድ መርከቦች ላይ ጥቃት ማድረሳቸው ይታወቃል፡፡
 
አሜሪካ እና ብሪታኒያ በበኩላቸው የነፃውን የንግድ ልውውጥ መስመር ለመጠበቅ እየሠራን ነው ብለዋል፡፡
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version