አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከጥር 3 እስከ 9 ቀን 2016 ዓ.ም በተደረገው ክትትል 3 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች መያዛቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ኮንትሮባንዱን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 14 ተጠርጣሪዎችና አራት ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል፡፡
የተያዙት ዕቃዎችም 130 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር የገቢ እና 169 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር የወጭ ኮንትሮባንድ ናቸው ተብሏል፡፡
ከኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ መካከልም አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድኃኒት፣ የመዋቢያ ዕቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የምግብ ዘይትና የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች እንደሚገኙበት ተጠቁሟል፡፡
በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የገቢ እና የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድም÷ አዲስ አበባ ኤርፖርት፣ ድሬድዋ እና አዋሽ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ ይዘዋል መባሉን የኮሚሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡