አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአንጋፋው ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ የቀብር ስነ-ስርዓት በመንበረ ጸባኦት ቅ/ሥላሴ ካቴድራል ተፈፀመ፡፡
ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ባደረበት ህመም በአሜሪካ ሕክምናውን ሲከታተል ቆይቶ ባለፈው ሳምንት ሕይወቱ ማለፉ ይታወቃል፡፡
በአሜሪካ የተለያዩ መርሃ ግብሮች ከተከናወኑ በኋላ ዛሬ ማለዳ የጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ አስከሬን አዲስ አበባ የገባ ሲሆን÷ የሙያ አድናቂዎቹ፣ የስራ ባልደረቦቹ እና የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውለታል።
በሚሊኒየም አዳራሽም የስንብት መርሐግብር ከተካሄደ በኋላ በመንበረ ጸባኦት ቅ/ሥላሴ ካቴድራል ቤተሰቦቹ፣ የሙያ አድናቂዎቹ፣ የስራ ባልደረቦቹ በተገኙበት የፍትሃት እና የቀብር ስነ ስርዓት ተካሂዷል፡፡
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በድጋሚ ለቤተሰቦቹ እና ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን ይመኛል።