አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፍሎሪዳው ገዢ ሮን ዴሳንቲስ ራሳቸውን ከፕሬዚዳንታዊ ውድድር በማግለል ዶናልድ ትራምፕን እንደሚደግፉ አስታውቀዋል፡፡
ሮን ዴሳንቲስ ከ2024 ፕሬዚዳንታዊ ፉክክር ራሳቸውን ያገለሉት በኒው ሃምፕሻየር ግዛት የመጀመሪያ ደረጃ ውድድር ሊደረግ ሁለት ቀናት ሲቀረው እንደሆነም ተመላክቷል፡፡
በተጨማሪም የወትሮው ተቀናቃኝ የፍሎሪዳው ገዢ ዶናልድ ትራምፕን እንደሚደግፉም በኤክስ (ትዊተር) የተንቀሳቃሽ ምስል አስመልክተዋል፡፡
ይህን ተከትሎም ሮን ዴሳንቲስ “ግልፅ የሆነ የድል መንገድ የለም” ሲሉም ሃሳባቸውን አጠናክረዋል፡፡
አክለውም፥ ትራምፕን የምደግፈው አብዛኞቹ የሪፐብሊካን ተቀዳሚ መራጮች ለዶናልድ ትራምፕ ሌላ እድል መስጠት እንደሚፈልጉ ግልጽ ስለሆነ ነው ብለዋል።
የፍሎሪዳው ገዢ ይህን ሃሳብ ያነሱት በትራምፕ በአዮዋ ካውከስ 30 በመቶ ነጥብ ሽንፈት ከገጠማቸው ከጥቂት ቀናት በኋላ እንደሆነም ነው የተጠቆመው።
ትራምፕ በ51 በመቶ ሲመሩ፤ ዴሳንቲስ ደግሞ በ21 በመቶ ሁለተኛ ተቀምጠው እንደነበር ዢኑዋ አስነብቧል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!