አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንገድ ደህንነት መድህን ፈንድ አገልግሎት በሶስተኛ ወገን መድህን ሽፋን ማስፈፀሚያ መመሪያ ላይ የሚታየውን ክፍተት ለማስተካከል ማሻሻያ እንደሚደረግ አስታወቀ።
የአገልግሎቱ ምክትል ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ፈቲያ ደድገባ÷ የመንግስትና የግል ህክምና ተቋማት በትራፊክ አደጋ ለተጎዱ ሰዎች እስከ 2 ሺህ ብር በነፃ አስቸኳይ የህክምና እና በትራፊክ አደጋ ለደረሰ የሞት አደጋ መንግስት ካሳ ይከፍላል የሚሉት ማሻሻያ እንደሚደረግባቸው ተናግረዋል።
ማሻሻያው የወቅቱን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እና የህብረተሰቡን አቅም ያገናዘበ መሆኑን ነው ምክትል ስራ አስፈጻሚዋ የጠቀሱት።
ማሻሻያው እንዲጸድቅ ለሚመለከተው አካል መላኩን ጠቅሰው፤ በቅርቡ ጸድቆ ተግባራዊ እንደሚደረግ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
በአልማዝ መኮንን