አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እስካሁን ያላትን የሻይ ተክል ልማት ወደ እጥፍ ለማሳደግ ዘንድሮ ከፍተኛ ሥራ እየተሰራ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ኢትዮጵያ እስካሁን ያላትን የሻይ ተክል ልማት ወደ እጥፍ ለማሳደግ ዘንድሮ ከፍተኛ ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል።
እስካሁን የተተከለው እንዳለ ሆኖ ምርቱን ለማሳደግ ከፍተኛ የችግኝ ዝግጅት እየተከናወነ እንደሚገኝም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡