Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአርብቶ አደር ቀን እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2016 ( ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአርብቶ አደር ቀን በደቡብ ኦሞ ዞን ዲመካ ከተማ ተከብሯል፡፡

“አርብቶ አደርነት የምስራቅ አፍሪካ ህብረ ቀለም” በሚል መሪ ሃሳብ የተከበረው የአርብቶ አደር ቀን በክልል ደረጃ ለ10ኛ ጊዜ መሆኑ ተመላክቷል።

ባለፉት ዓመታት በአርብቶ አደር አካባቢ ያሉትን የተፈጥሮ ፀጋዎች ወደ ውጤት ለመቀየር በተደረገው እንቅስቃሴ አበረታች ለውጥ መመዝገቡ በስነ-ስርዓት ላይ ተገልጿል ።

በተለይ በመስኖ ልማት አርብቶ አደሩ የምግብ ዋስትናውን ከማረጋገጥ ባለፈ ዘላቂ ኢኮኖሚና ሀብት የሚያካብትበት እድል መፈጠሩም ተወስቷል።

የዘንድሮው የአርብቶ አደሮች ቀን የተሻለ ኢኮኖሚና ለውጥ እንዲመዘገብ የጋራ አቋም የሚያዝበትና ልምድ የሚወሰድበት እንደሆነም ተመላክቷል።

በበዓሉ ላይ የደቡብ ኦሞ ዞን የአርብቶ አደር ማህበረሰብ ተወካዮች የተሳተፉ ሲሆን÷ከአጎራባች ሀገራት ከኬንያ ቱርካና እና ከደቡብ ሱዳን የአርብቶ አደር ተወካዮች ታድመዋል፡፡

 
 #Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version