የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደሮች ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ በማሳተፍ ለሀገራዊ ምክክሩ አስተዋጽኦ ማበርከት አለባቸው – መስፍን አርዓያ(ፕ/ር)

By Meseret Awoke

January 18, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በውጭ ሀገራት የሚገኙ አምባሳደሮች እና ሚሲዮኖች ዳያስፖራውንና ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ በማሳተፍ ለሀገራዊ ምክክሩ አስተዋጽኦ ማበርከት አለባቸው ሲሉ የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ሰብሳቢ መስፍን አርአያ (ፕ/ር) ገለጹ፡፡

አምባሳደሮች እና የሚሲዮን መሪዎች በብሄራዊ ውይይት ሒደት ላይ ተወያይተዋል፡፡

መስፍን አርአያ(ፕ/ር) በዚህ ወቅት÷ለኢትዮጵያ አምባሳደሮች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ስለ ኮሚሽኑ ተግባራት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በውጭ ሀገራት የሚገኙ ሚሲዮኖች የኢትዮጵያን ዳያስፖራዎች እና ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ በማሳተፍ ለሀገራዊ ምክክሩ ሒደት መሳካት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ማበርከት አለባቸው ብለዋል።

ውይይቱን የመሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ መሆናቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡ (FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!