የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደሮች በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ድርድር እና በዓባይ ወንዝ አጠቃቀም ላይ ተወያዩ

By Meseret Awoke

January 18, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ሀገራት የኢትዮጵያ አምባሳደሮች በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ድርድር እና በዓባይ ወንዝ አጠቃቀም ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ የኢትዮጵያ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዋና ተደራዳሪ አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) (ኢ/ር) እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ህግ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ረታ አለሙ በኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን መካከል የተካሄደውን ተከታታይ የሦስትዮሽ ድርድር አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አምባሳደሮቹ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ውሃ ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ የሆነ አጠቃቀም መርሕ ላይ ያላትን እምነት እና በመሠረታዊ መርሆዎች መግለጫ ላይ የተመለከቱትን መብቶች እና ግዴታዎች አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ የሁሉንም የተፋሰሱ ሀገራት ጥቅም ለማስከበር ያላትን ጽኑ አቋም መግለጻቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡ (FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!