የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች አውሮፕላን በመቀሌ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ካረፈ በኋላ ከበረራ መስመር የመንሸራተት ችግር እንዳጋጠመው አስታወቀ

By Melaku Gedif

January 18, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች አውሮፕላን በመቀሌ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ካረፈ በኋላ ከበረራ መስመር የመንሸራተት ችግር እንዳጋጠመው አስታወቀ፡፡

በጉዳቱ በመንገደኞች እና በበረራ ሰራተኞች ላይ ያጋጠመ ምንም አይነት ጉዳት አለመኖሩንም አየር መንገዱ አረጋግጧል፡፡

የበረራ ቁጥር ET106/18 የሆነው የመንገደኞች አውሮፕላን ከአዲስ አበባ ከቀኑ 6፡30 ተነስቶ 8፡10 ላይ መቀሌ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ መድረሱም ተመላክቷል፡፡

የአደጋው ምክንያት እየተጣራ መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጹ የገለጸው አየር መንገዱ÷ በተፈጠረው ክስተት ለተስተጓጎሉ መንገደኞችም ይቅርታ ጠይቋል፡፡