የሀገር ውስጥ ዜና

አዲሱ የአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲ በዘርፉ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን እንደሚፈታ ተገለጸ

By Shambel Mihret

January 17, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲሱ የአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲ እና የብሄራዊ ተኪ ምርት ስትራቴጂው በዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን እንደሚቀርፍ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

በአዲሱ የአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲ የብሄራዊ ተኪ ምርት እስትራቴጂ ላይ የፌደራል እና የሐረሪ ክልል አመራሮች መክረዋል፡፡

አቶ ኦርዲን በመድረኩ እንዳሉት÷ የአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲ እና የብሄራዊ ተኪ ምርት ስትራቴጂው ከዚህ ቀደም በኢንዱስትሪ ልማት ላይ ሲስተዋሉ የቆዩ ክፍተቶችን ይቀርፋል፡፡

ፖሊሲውን ለመተግበር የሚያስችሉ ተቋማትን መገንባት እንደሚያስፈልግም ማስገንዘባቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

በክልሉ የአምራች ኢንዱስትሪ ሽግግር ፖሊሲ ተግባራዊ እንዲሆን ሁሉም በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባም ነው የገለጹት፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዲኤታ ሀሰን መሐመድ በበኩላቸው÷ ፖሊሲው የሥራ እድልን ለማስፋት፣ የውጭ ኢንቨስትመንትን ለማጎልበት፣ የወጪና የገቢ ምርቶችን ለማመጣጠን ከፍተኛ ፋይዳ አለው ብለዋል፡፡