Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

“ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን” ድጋፉን እንዲያጠናክር ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን” በኢትዮጵያ እያደረገ ያለውን የልማት ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠየቀ፡፡

በዳቮስ እየተካሄደ ከሚገኘው የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ጎን ለጎን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከ“ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ” መሥራች እና ሊቀ-መንበር ቢል ጌትስ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም÷ “ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን” በጤና፣ ግብርና እና በሰው ሐብት ልማት ዘርፎች በኢትዮጵያ እያደረገ ለሚገኘው ድጋፍ አቶ ደመቀ አመስግነዋል፡፡

ፋውንዴሽኑ የምጣኔ ሐብት ዕድገትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያጠናክርም አቶ ደመቀ መጠየቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

ቢል ጌትስ በበኩላቸው÷ የዜጎችን ሕይወት ለመለወጥ የሚያስችሉ የልማት ሥራዎችን አጠናክረው መሥራታቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

ፋውንዴሽኑ የኢትዮጵያ መንግሥት ቅድሚያ በሚሰጣቸው የልማት ዘርፎች ላይ በመሠማራት ላለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት የሰዎችን ኑሮ የለወጡ ሥራዎችን ሲሠራ ቆይቷል፡፡

Exit mobile version