Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ደቡብ ኢትዮጵያና ጋምቤላ ክልሎችን ከጎበኙ ቱሪስቶች 100 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ እና ጋምቤላ ክልሎች የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ከጎበኙ ቱሪስቶች 99 ሚሊየን 800 ሺህ ብር መገኘቱን የየክልሎቹ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮዎች አስታወቁ፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ፍሬሕይወት ዱባለ እንዳሉት÷ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ ክልሉን ከጎበኙ 3 ሚሊየን 229 ሺህ 75 ቱሪስቶች 71 ሚሊየን ብር ገቢ ተገኝቷል፡፡

ከቱሪስቶቹ መካከል 4 ሺህ 75 የሚሆኑት የውጭ ሀገራት ዜግነት ያላቸው ጎብኚዎች መሆናቸውንም አብራርተዋል፡፡

በተመሳሳይ ክልሉን ከጎበኙ 8 ሺህ ቱሪስቶች 28 ሚሊየን 800 ሺህ ብር ገቢ መገኘቱን የጋምቤላ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ የቱሪስት መዳረሻ ጥናትና ልማት ባለሙያ ደርባቸው ሸዋለም ተናግረዋል፡፡

ከወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታዎች ጋር የተያያዙ ችግሮች ማጋጠማቸው እንዲሁም የበጀት እጥረትና የክልሉን የቱሪዝም ሐብት በአግባቡ ማስተዋወቅ አለመቻል አፈጻጸሙ አጥጋቢ እንዳይሆን እንዳደረገውም አንስተዋል፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጎብኚዎች የቆይታ ጊዜ በአማካይ ሥድስት ቀን ሲሆን በጋምቤላ ክልል ደግሞ ሦስት ቀን መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

Exit mobile version