Fana: At a Speed of Life!

አፕል ቀዳሚ የስማርት ስልክ አምራችነቱን ስፍራ ከሳምሰንግ ተረከበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ12 ዓመታት በሳምሰንግ ተይዞ የቆየውን ዓለም አቀፍ የስማርት ስልክ አምራችነትን የቀዳሚነት ደረጃ አፕል ኩባንያ ተረከበ።
 
የአሜሪካው ግዙፍ የስማርት ስልክ አምራች ኩባንያ አፕል ባለፈው ዓመት ከአምስት ጊዜ በላይ ምርቶቹን በባህር ትራንፖርት ለዓለም ገበያ ማቅረቡን የዓለም አቀፍ ዳታ ኮርፖሬሽን መረጃ አመላክቷል።
ሳምሰንግ በአንፃሩ ከቻይና ስልክ አምራቾች ዢያኦሚ፣ ኦፖ እና ትራንሺን ጋር የ19 ነጥብ 4 በመቶ የገበያ ድርሻን መውሰዱ ተነግሯል።
 
በስማርት ስልክ ገበያው አናት ላይ የተቀመጠው አፕል ባለፈው ዓመት ከ 234 ሚሊየን በላይ ስልኮችን መሸጡን አይዲሲ አስታውቋል፡፡
ባለፈው ዓመት ወደ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን የሚጠጉ ስማርት ስልኮች መሸጣቸውን የገለፀው ዓለም አቀፉ ዳታ ኮርፖሬሽን፤ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ3 በመቶ በላይ ቅናሽ ማሳየቱን አመላክቷል፡፡
ይህም በአስር ዓመታት ውስጥ ከነበረው የሽያጭ መጠን ጋር ሲተያይ ዝቅተኛው መሆኑን ነው የገለጸው፡፡
ብዙ ሸማቾች ከኢኮኖሚያዊ ችግሮች እና ከከፍተኛ የወለድ ምጣኔ የተነሳ እጅ እያጠራቸው መምጣቱ ተነግሯል።
ይሁንና በዚህ ዓመት ገበያው ሊያገግም እንደሚችል ባለሙያዎች መተንበያቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡ (FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.