አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የተዘጋባት በር በመከፈቱ ለዘርፉ ትልቅ ዕድል መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ የሴክተር አፈጻጸም በወላይታ ሶዶ ከተማ እየገመገመ ነው፡፡
ዓለሙ ስሜ(ዶ/ር) በወቅቱ፥ ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ የሁሉም ዘርፎች ደም ስር በመሆኑ በጋራ ልንሠራ ይገባል ነው ያሉት።
በዚህም ባለፉት ጊዜያት በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የተሳኩ ተግባራት መፈጸማቸውን ገልጸዋል፡፡
ሆኖም ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን በጊዜ የለንም መንፈስ በመስራት ኢትዮጵያ ከዕዳ ወደ ምንዳ ለመሻገር የተለመችውን ተግባር ዕውን ለማድረግ አቋም መያዝ እንደሚገባ አመልክተዋል።
ወቅቱ ኢትዮጵያን ከእዳ ወደ ምንዳ የምናሻግርበት እንደመሆኑ አሁን ያለውን እዳ ሽረን ወደ ምንዳ ለመሻገር የትራንስፖርት ዘርፉ ሚናው የጎላ ነውም ብለዋል።
ኢትዮጵያ በአንድ ወቅት አጠቃላይ የምሥራቅ አፍሪካ ባሕር በር የምትቆጣጠር ሀያል ሀገር እንደነበረች የገለጹት ሚኒስትሩ፥ በተለያዩ ስህተቶች ባለ ግዙፍ ሀብት ባለቤት ሀገር ኢትዮጵያን በመሬት ብቻ የታጠረች እንድትሆን ማድረጉን ይገልፃሉ።
በዚህ ቁጭት መሃል ከሶማሊላንድ ጋር የተደረሰው የባህር በር የመጠቀም ስምምነት የተዘጋ በር ላላት ኢትዮጵያ መተንፈሻ የሚሰጥ እንደሆነም ነው የተናገሩት።
ሚኒስትሩ አክለውም፥ የባህር በር ማግኘታችን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍን በእጅጉ እንደሚያሳድግና ትልቅ ዕድል መሆኑንም ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በበኩላቸው፥ እንደክልል የኢንቨስትመንት አቅማችንን ሙሉ ለሙሉ ማልማት ብንችል ለክልላችን ብቻ ሳይሆን ለሀገር የሚተርፍ አቅም አለን ብለዋል።
በዚህም በመንገድ እና ውሃ ትራንስፖርት ላይ በጋራ ብንሠራ እንደክልል እምቅ አቅም አለንም ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡
የኤክስፖርት ሰብሎች፣ አትክልትና ፍራፍሬ ከሀገር አልፎ ለውጭ ምንዛሬ የሚያስገኝ ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ የመንገድ መሠረተ ልማት ትልቅ እንቅፋት እየሆነ መቆየቱን አስረድተዋል።
በዚህም በክልሉ የሚመረቱ የፍራፍሬ የጓሮ አትክልት እና የዓሳ ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ሳይበላሽ ለማቅረብ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ላይ መሥራት ወሳኝ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በመለስ ታደለ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡ (FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!