Fana: At a Speed of Life!

ሰው ሠራሽ አስተውኅሎት 60 በመቶ ያደጉ ሀገራት ሥራ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰው ሠራሽ አስተውኅሎት ባደጉ ሀገራት 60 በመቶ በሚሆነው ሥራ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖውን እንደሚያሳርፍ ተነግሯል፡፡

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጂኦርጄቫ ከአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ጋር ባደረጉት ቆይታ ይህን ያሉት በስዊዘርላንድ ዳቮስ ወደሚካሄደው ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም ከመሄዳቸው በፊት መሆኑን ሲጂቲኤን አስነብቧል።

ዳይሬክተሯ ÷ ይህንኑ ጉዳይ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ዕሁድ ባወጣው ሪፖርት ማመላከቱንም ጠቁመዋል፡፡

አዲሱ ልምምድ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት 40 በመቶ በሚሆነው ኢኮኖሚ ተፅዕኖ እንደሚያሳርፍና ባላደጉት ደግሞ 26 በመቶ በሚሆነው ገበያቸው ላይ ጣልቃ እንደሚገባም አያይዘው ገልጸዋል፡፡

በዚህም ቴክኖሎጂው ግማሽ በሚያኅል መሥራት የሚችል የዓለማችን የሰው ሐብት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖውን ሲያሳርፍ የተቀሩት ግን የተሻለ ምርታማነትን ስለሚያገኙ ከአዲሱ ልምምድ ተጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉም ነው የተባለው።

በመጨረሻም እንደ ክሪስታሊና ጂኦርጄቫ ገለጻ ÷ አዲሱ ልምምድ የሰዎችን ሥራ መተካቱ አስፈሪ ቢመስልም አይቀሬ እና ሁሉም ራሱ ከቴክኖሎጂው ጋር ካስማማ ተጠቃሚ ሊሆን የሚችልበትን ትልቅ ዕድል አለ፡፡

#ArtificialIntelligence

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡ (FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.