አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ መካከለኛ መጠን ያለው የባለስቲክ ሚሳኤል በተሳካ ሁኔታ መሞከሯን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል፡፡
ሙከራው የባላስቲክ ሚሳኤሉን የአረር ተሸካሚ ክፍል እንቅስቃሴን ለመመልከት እና ተንቀሳቃሽ ሞተሮችን ብቃት ለማረጋገጥ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ፒዮንግያንግ የሚሳኤል ሙከራው የጎረቤት ሀገራትን ደህንነት ያልነካ እና ከቀጠናዊው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው መሆኑን ገልፃለች፡፡
የጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ሀይሎችም ባላስቲካ ሚሳዔሉ ከጃፓን የኢኮኖሚ ቀጠና ውጭ መውደቁን አረጋግጠዋል፡፡
ሚሳኤሉ ሰሜን ኮሪያ በ2024 ለመጀመሪያ ጊዜ ያስወነጨፈችው አህጉር አቋራጭ ባላስቲክ ሚሳኤል ሲሆን ሀገሪቱ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ለመጨረሻ ጊዜ ታህሳስ 18 ቀን 2023 ሃውሶንግ -18 የተባለውን የባላስቲክ ሜሳኤል ማስወንጨፏን ስፑቲንክ ኢንተርናሽናል ዘግቧል፡፡