አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሰላም መጠበቅ፣ ለዴሞክራሲ ማበብና ለልማት መጎልበት የክልሉ ሕዝብ ትጋቱን አጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ገለጹ፡፡
የሃላባ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “ሴራ” በዓል ማጠቃለያ መርሐ ግብር በሃላባ ቁሊቶ ከተማ እየተከበረ ነው፡፡
በበዓሉ የተገኙት አቶ እንዳሻው ጣሰው ÷ የሴራን በዓል ለሚቀጥለው ትውልድ ለማሻገር በተጠናከረ መልኩ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል ።
ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር በሚደረግ ጥረት ሁሉም የበኩሉን ሚና መጫወት እንዳለበትም ነው ያስገነዘቡት፡፡
ለሰላም መጠበቅ፣ ለዴሞክራሲ ማበብና ለልማት መጎልበትም የክልሉ ሕዝብ ትጋቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙሁዲን ሁሴን በበኩላቸው እንዳሉት ÷የሃላባ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “ሴራ” ብዝሃ ባህልና እሴቶችን በውስጡ የያዘ ትልቅ በዓል ነው፡፡
እንደ ሀገር ያዳበርናቸውን የሰላም እና የአብሮነት እሴቶቻችንን አጎልብተን መቀጠል አለብንም ብለዋል ።
በብርሃኑ በጋሻው
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡ (FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!