Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ብሪታንያ ለዩክሬን የምታደርገውን ድጋፍ ወደ 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ፓውንድ ልታሳድግ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሪታንያ ለዩክሬን የምታደርገውን ወታደራዊ ድጋፍ ወደ 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ፓውንድ ልታሳድግ መሆኑን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ አስታውቀዋል፡፡
 
ድጋፉ ከሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት መቀስቀስ በኋላ የሚደረግ የዓመቱ ትልቅ መነሳሳት ነው ተብሏል፡፡
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያስታወቁት በሀገሪቱ ጉብኝት ባደረጉት ወቅት ሲሆን÷ የረጅም ጊዜ የደህንነት ድጋፍ ዙሪያም አዲስ ስምምነት እንደሚፈራረሙ ተገልጿል።
 
የድጋፍ ማዕቀፉ ለዩክሬን የረዥም ርቀት ሚሳኤሎች፣ የአየር መከላከያ እና የመድፍ ተተኳሾችን ያካተተ መሆኑን ባለስልጣናት ተናግረዋል።
 
200 ሚሊየን ፓውንድ የሚጠጋው ገንዘብ ለሰው አልባ ድሮኖች የሚውል ሲሆን÷ አብዛኛዎቹም በእንግሊዝ የሚሰሩ መሆናቸው ተመላክቷል።
 
ባለሥልጣናቱ አክለውም ወታደራዊ ማዕቀፉ÷ ከፈረንጆቹ ሚያዚያ ወር ለሚጀምረው የፋይናንስ ዓመት ከየትኛውም ሀገር ከፍተኛውን ሰው አልባ ድሮኖች ለዩክሬን እንደሚያቀርብ ተናግረዋል።
 
ይሁን እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለበርካታ ዓመታት የሚቆይ የፋይናንስ ድጋፍ ላለማድረግ መወሰናቸውንም በግልፅ ማብራራታቸው እንደተገለጸ ቢቢሲ ዘግቧል።
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡ FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version