Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ወጣቱ ትውልድ የጋራ ነገን መገንባት እንዳለበት ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ወጣቱ ትውልድ የጋራ ማንነቶችን በማወቅ የጋራ ነገን መገንባት እንዳለበት ተመላከተ።
 
“የምሁራን ወጣቶች ሚና ለሀገረ መንግሥት ግንባታ” በሚል መሪ ሐሳብ በብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ዋና ጽሕፈት ቤት የተዘጋጀ የፓናል ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
 
በውይይቱም ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ወጣት ምሁራን እየተሳተፉነው፡፡
 
የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በውይይቱ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር÷ ወጣቱ ትውልድ የጋራ ማንነቶችን ማወቅና መገንባት ይጠበቅበታል፤ ይህን ማድረግ ሲቻልም የጋራ ነገን መገንባት ይቻላል ብለዋል፡፡
 
ሀገር በቅብብሎሽ የምናስቀጥላት በመሆኗ ወጣቱ ትውልድ የሀገር ተረካቢ ብቻ ሳይሆን የሀገር ባለቤት በመሆኑ ለሀገረ መንግስት ግንባታ ሚናው የጎላ ስለመሆኑ አስገንዝበዋል፡፡
 
የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ምክትል ፕሬዚዳንት ፈዲላ ቢያ በበኩላቸው÷ ወጣቶች ነገሮችን በቀላሉ ከመፈረጅ ይልቅ በሚዛናዊነት በማየት ለሀገረ መንግስት ግንባታ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡
 
ወጣቱ ለሀገረ መንግስት ግንባታ ከጊዜ ጋር አብሮ መሄድና ውሳኔ ሰጭ ሆኖ መቀጠል እንዳለበት ያመላከቱት ደግሞበሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ረዳት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ዴዔታ ረ/ፕሮፌሰር ምህረቱ ሻንቆ ናቸው፡፡
 
በሳሙኤል ወርቃየሁ
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version