Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በባሕር በር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በጅማ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በባሕር በር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በጅማ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የተፈራረሙት ሥምምነት ለቀጣናዊ ሰላምና ትስስር እንዲሁም ልማት ጉልህ ፋይዳ እንዳለው የሚገልፁ ጥናቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በጥናቱ ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት ከሶማሊላንድ ጋር የተፈራረመችው ስምምነት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ተመላክቷል፡፡

የውጭ ሀገራት የኢንቨስትመንት ፍላጎት እንዲጨምር እና ከብሄራዊ ደህንነት አንፃርም ጉልህ ፋይዳ ያለው መሆኑ በጥናቱ ተጠቅሷል፡፡

ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርሕ አብሮ የመልማት ጥያቄ ማቅረቧ ፍትሃዊና የማንንም ጥቅም የሚጋፋ አለመሆኑም ተጠቁሟል፡፡

በጥናቱ ላይ የተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን መሳተፋቸው ተገልጿል፡፡

በሙክታር ጠሃ

Exit mobile version