አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው 10ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቻል ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ አቻ ተለያይቷል፡፡
9፡00 ላይ ሐዋሳ ከተማን የገጠመው መቻል 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡
የመቻልን ጎሎችም ምንይሉ ወንድሙ እና ከንዓን ማርክነህ ሲያስቆጥሩ÷ የሐዋሳ ከተማን ብቸኛ ጎል አሊ ሱለይማን አስቆጥሯል፡፡
ውጤቱን ተከትሎም መቻል ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በእኩል 23 ነጥብ ፕሪሚየር ሊጉን መምራት ሲችል÷ ሐዋሳ ከተማ በነበረበት 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
እንዲሁም 12፡00 ላይ በተደረገው ሌላ የጨዋታ መርሐ-ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀድያ ሆሳዕናን አስተናግዶ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይቷል፡፡
በውጤቱን ተከትሎም ፈረሰኞቹ በ18 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ÷ ሀድያ ሆሳዕና ደግሞ አንድ ደረጃ አሻሽሎ 9ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡