አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የየመን ሁቲ አማጺዎች በቀይ ባህር መተላለፊያ ላይ ከመቼውም ጊዜ ከፍ ያለ በበርካታ ሚሳኤል እና የሰው አልባ አውሮፕላኖች የታገዘ ጥቃት መፈጸማቸው ተገለጸ፡፡
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ጥቃቱን “ውስብስብ ተልዕኮ” ሲል የጠራው ሲሆን ነገር ግን መቀልበስ መቻሉን ገልጿል።
የመካከለኛው ምስራቅ እና መካከለኛው እስያ ተልዕኮዎችን በበላይነት የሚቆጣጠረው የአሜሪካ ማዕከላዊ አዛዥ ጥቃቱ በትናንትናው ዕለት መሞከሩን አስታውቋል፡፡
በርካታ ፀረ-መርከብ ሚሳኤሎች እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት የሁቲ አማጺያን ከሚቆጣጠራቸው የየመን አካባቢዎች ወደ ደቡባዊ ቀይ ባህር መሰንዘራቸውን አስታውቋል።
18 የአንድ አቅጣጫ ጥቃት አድራሽ ሰው አልባ አውሮፕላኖች፣ ሁለት ክሩዝ ሚሳኤሎች እና አንድ ባለስቲክ ሚሳኤል በአሜሪካ እና እንግሊዝ ጦር መርከቦች ተመትተው መውደቃቸው መነገሩን አር ቲ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!