Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከ12 ሺህ በላይ የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎት ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ ከ12 ሺህ ለሚልቁ የአገልግሎት ጥያቄዎች የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎት መስጠቱን የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት አስታወቀ፡፡

አገልግሎቱ የተሰጠው በምርት ጥራት የፍተሻ ላቦራቶሪ፣ በወጪና ገቢ ምርት ኢንስፔክሽን እንዲሁም በሰርቲፊኬሽን መሆኑን የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መዓዛ አበራ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

በጂቡቲ ወደብ በኩል ወደ ሀገር ውስጥ ለሚጓጓዝ ከ509 ሺህ በላይ ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ እና የተለያዩ የጅምላ ጭነት ምርቶች የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎት መሰጠቱንም ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም ከ16 ሚሊየን በላይ ሊትር የምግብ ዘይት ኢንስፔክሽን አገልግሎቶች በመስጠት ጥራት ያለው ምርት ለሕብረተሰቡ እንዲቀርብ መደረጉንም ነው ያመላከቱት፡፡

በዚህም የሸማቹን ጤና እና የአካባቢ ደኅንነት ለመጠበቅ በሚከናወኑ ሥራዎች ድርጅቱ የበኩሉን እየተወጣ ስለመሆኑ ጠቅሰዋል፡፡

ድርጅቱ በኢትዮጵያ 8 ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶችን በማደራጀት እና በጅቡቲ ወደብ በሚገኘው ቅርንጫፉ የጥራት ማረጋገጥ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝም አስታውቀዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version