የሀገር ውስጥ ዜና

ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርና ሁዋዌ ኢትዮጵያ በጋራ በሚሰሯቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

By Meseret Awoke

January 10, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከሁዋዌ ኢትዮጵያ ጋር አነስተኛ የሀይል አቅርቦት ስራዎችን የሚያቀላጥፉ ቴክኖሎጂዎችን በሚመለከት በጋራ ስለሚሰሯቸው ጉዳዮች ተወያይተዋል፡፡

ሁዋዌ ኢትዮጵያ ለገበያ የሚያቀርባቸውና አነስተኛ የኃይል አቅርቦት ስራዎችን የሚያቀላጥፉ ቴክኖሎጂዎች፣ ለግለሰብ መኖሪያ ቤት፣ ከዋናው የኤሌክትሪክ መስመር ርቀው ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችና ለቢዝነስ ተቋማት አገልግሎት የሚሰጡ አዳዲስ የኃይል አቅርቦት አማራጭ ቴክኖሎጂዎችን የሚያስተዋውቅ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ሁዋዌ የዲጂታል ፓዎር ቴክኖሎጂ አገልግሎቶችን በማቅረብ ረገድ በሌሎች ሀገራት ያለውን ልምድና ተሞክሮ በኢትዮጵያም ለማስፋፋት ያለውን ዝግጁነት አስመልክቶ የድርጅቱ ባለሙያ ገለፃ አድርገዋል፡፡

የሁዋዌ ዲጂታል ፓዎር ቴክኖሎጂ አገልግሎቶችን በስፋት ሊያስተዋውቅ የሚችል፣ የዘርፍ ተቋማትን፣ ክልሎችንና የግል ኢነርጂ ቴክኖሎጂ አቅራቢ ተቋማትን የሚያሳትፍ አውደ ርዕይ በመጋቢት ወር ውስጥ ሊዘጋጅ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

አውደርዕዩ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና በሁዋዌ ኢትዮጵያ ትብብር የሚካሄድ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

በውይይቱ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር)፣ የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር ኢ/ር) እንዲሁም ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና ከነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን የመጡ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!