Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በመዲናዋ 30 የእግረኛ ማቋረጫ ተሻጋሪ ድልድዮችና መተላለፊያዎች ሊገነቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በቀላል ባቡርና ቀለበት መንገዶች 30 የእግረኛ ማቋረጫ ተሻጋሪ ድልድዮችና መተላለፊያዎች ሊገነቡ መሆኑን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ።

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ እያሱ ሶሎሞን ÷ ባለሥልጣኑ የከተማዋን አጠቃላይ የትራፊክ እንቅስቃሴ ምቹ፣ ቀልጣፋና ደኅንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ በርካታ የመንገድ ግንባታ ሥራዎችን እያከናወነ ነው ብለዋል።

በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር በሚያልፍባቸውና ውስጠኛው ቀለበት መንገድ ተብለው በሚጠሩ ቦታዎች ላይ መሸጋገሪያ ድልድዮችና መተላለፊያዎች ባለመኖራቸው እግረኞች ለትራፊክ አደጋ እየተጋለጡና መንገድ ለማቋረጥ ረዥም ርቀት ለመጓዝ እንደሚገደዱ ተናግረዋል።

ተሻጋሪ ድልድዮቹና መተላለፊያ መስመሮቹ ከመሬት በላይ እንዲሁም በመሬት ውስጥ እንደሚገነቡ መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የእግረኛ ተሻጋሪ ድልድዮቹ ሐና ማርያም፣ ኃይሌ ጋርመንት፣ ሳሪስ ሐኪም ማሞ ሰፈር፣ አደይ አበባ፣ ጉርድ ሾላ፣ አውቶቡስ ተራና አብነት አካባቢ እንዲሁም በሌሎችም አካባቢዎች እንደሚገነቡ ተመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version