አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሂዝቦላህ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዠ ዊሳም ታዊል በእስራዔል ጥቃት መገደሉ ተሰምቷል፡፡
ወታደራዊ አዛዡ እስራዔል በደቡባዊ ሊባኖስ በፈጸመችው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ነው የተገደለው፡፡
የድሮን ጥቃቱ ዊሳም ታዊል እና ሌሎች የሂዝቦላህ አባላትን በያዘች መኪና ላይ መፈጸሙን ሬውተርስ የአይን እማኞችን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
በከፍተኛ ወታደራዊ አዛዡ ላይ የተፈጸመው ጥቃት አሰቃቂ እንደነበርም በሥፍራው የነበሩ የጸጥታ አካላት ተናግረዋል፡፡
ሂዝቦላህ በበኩሉ÷ ዊሳም ታዊል የተባለው ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ ሕይወቱ ማለፉን ቢያረጋግጥም ሕይወቱ ያለፈበትን ዝርዝር ምክንያት ከመጥቀስ መቆጠቡ ተመላክቷል፡፡