Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በእስራዔል ሃማስ ጦርነት 1 ነጥብ 9 ሚሊየን ፍልስጤማውያን ከጋዛ ተፈናቅለዋል – ተመድ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእስራዔል እና ሃማስ ጦርነት ምክንያት እስካሁን 1 ነጥብ 9 ሚሊየን ፍልስጤማውያን ከጋዛ መፈናቀላቸውን የተባበሩት መንስግታት ድርጅት (ተመድ) አስታወቀ፡፡

ተፈናቃዮቹ ሰሜን ጋዛ እና ጋዛን ጨምሮ ከአምስት ግዛቶች የተወጣጡ ሲሆን ተመድ ባዘጋጀላቸው ጊዜያዊ መጠለያዎች እንደሚገኙ ተመላክቷል፡፡

94ኛ ቀኑን ባስቆጠረው ጦርነት እስካሁን 22 ሺህ 835 ፍልስጤማውያን ሲሞቱ ከ58 ሺህ 416 በላይ የሚሆኑት ደግሞ መቁሰላቸው ተገልጿል፡፡

ከሰሞኑ የዓለም ጤና ድርጅት ተፈናቃዮችን ለመርዳት የሚያስችሉ የህክምና ቁሳቁሶችን ወደ ሰሜናዊ ጋዛ ለማድረስ ጥረት ቢያደርግም የፀጥታ ዋስትና ባለማግኘቱ የእርዳታ ተልዕኮውን ለማቋረጥ መገደዱም ተስምቷል፡፡

በጦርነቱ ምክንያት እየተከሰተ ያለው ሰብዓዊ ቀውስ በተባባሰበት ሁኔታ እስራዓል በጋዛ የምታደርገውን ጦርነት አጠናክራ መቀጠሏን ቲአርቲ ዎርልድ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version