አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2024 የዱባይ እና ዥያሜን ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸንፈዋል፡፡
በዱባይ በወንዶች የተካሄደውን ውድድር አትሌት አዲሱ ጎበና ሲያሸንፍ÷ ለሚ ዱሜቻ 2ኛ፣ ደጀኔ መገርሳ 3ኛ እንዲሁም አብዲ ፉፋ 4ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡
በዚሁ የውድድር መርሐ-ግብር÷ አትሌት አንተን አየሁ ዳኛቸው 6ኛ፣ ሌንጮ ተስፋዬ 8ኛ፣ ባየልኝ ተሻገር 9ኛ እና አበባው ደሴ 10ኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡
እንዲሁም በሴቶች የተካሄደው የማራቶን ውድድር በአትሌት ትዕግስት ከተማ አሸናፊነት መጠናቀቁን በዱባይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡
በዚሁ ውድድር አትሌት ሩቲ አጋ 2ኛ፣ ደራ ዲዳ 3ኛ፣ ፎዚያ ጀማል 5ኛ፣ ሽታዬ እሸቴ 6ኛ፣ አታለል አንሙት 7ኛ፣ ቤተልሔም አፈንጉስ 8ኛ፣ እመቤት ንጉሴ 9ኛ እና ኑሪት ሽመልስ 10ኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡
በተመሳሳይ በቻይና ዥያሜን በተደረገው የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡
በወንዶች አሰፋ ቦኪ 2 ሰዓት ከ06 ደቂቃ ከ46 ሴኮንድ በመግባት የወርቅ ሜዳሊያ ሲያሸንፍ ኬንያዊው ፌሊክስ ኪፕቶ 2ኛ እንዲሁም ሞሮኳዊው ኢል ጎምሪ 3ኛደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል፡፡
በሴቶች ደግሞ በቀለች ጉደታ 2 ሰዓት ከ22 ደቂቃ ከ54 ሴኮንድ በመግባት ስታሸንፍ ሞሮኳዊቷ ፋጢማ ኤዝሃራ ሁለተኛ እንዲሁም ቻይናዊቷ ዛንግ ዱሹን ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል፡፡
የዥያሜን ማራቶን በፈረንጆቹ 2021 ከዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃን ያገኘ ሲሆን በቻይና ከሻንጋይ ማራቶን በመቀጠል ትልቁ ውድድር ሆኖ ተምዝግቧል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!