አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለገና በዓል ከታረደ በሬ 6 ነጥብ 11 ግራም ወርቅ መገኘቱ ተሰምቷል፡፡
በወላይታ ሶዶ ከተማ ለገና በዓል ቅርጫ ከታረደው በሬ ውስጥ ነው 6 ነጥብ 11 ግራም ወርቅ የተገኘው።
በወላይታ ባህል ለበዓል “አሞ” ወይም ቅርጫ ማረድ የተለመደ ሲሆን÷ ነገ ለሚከበረው የገና በዓል በታረደው የቅርጫ በሬ ውስጥም ወርቅ መገኘቱ ተገልጿል፡፡
የቅርጫ አባላቱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት ፥ የተገኘው ወርቅ የገና በዓል ስጦታ ነው።
በማህሌት ኡኩሞ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!