Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በምሥራቅ ሸዋ ዞን ሎሜ ወረዳ በክረምት በጎ ፍቃድ የተገነቡ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 26 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ሎሜ ወረዳ በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ያስገነባቸውን መኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች አስረክቧል።
በርክክብ መርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙት የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴዔታ ጥሩማር አባተ፥ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አንድነትን ከማጠናከር ባለፈ የመደጋገፍ ባሕልን የሚያሳድግ ነው ብለዋል፡፡
የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ትኩረት እንዲሰጠው አቅጣጫ መቀመጡን ተከትሎ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የበጎ ፍቃድ ሥራዎችን ሲከውን መቆየቱንም አንስተዋል።
በዚህም የዐቅመ ደካማ ዜጎችን ቤቶች በማደስ ፣ በአረንጓዴ ዐሻራ ልማት እና በሌሎች መሥኮች ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ሎሜ ወረዳ በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎቱ ተጠቃሚ ለሆኑ 10 አባ ወራዎች ደረጃቸውን የጠበቁና መሠረታዊ ቁሳቁስ የተሟሉላቸው መኖሪያ ቤቶች ተላልፈዋል፡፡
ለቤቶቹ ግንባታ ከ5 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ መደረጉም ተመላክቷል።
ለአባ ወራዎቹ የበዓል መዋያ የሚሆን የፍጆታ ዕቃና የገንዘብ ድጋፍ እንደተደረገላቸውም ተገልጿል፡፡
በወንድሙ አዱኛ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version