አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 26 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቻይናዋ ቾንቺን ከተማ አስተዳደር ኮንግረስ ሊቀመንበር ዣዎ ሺቺንግ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነት በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ ወቅት ÷ዣዎ ሺቺንግ እና ልዑካቸው አዲስ አበባ ከበርካታ የቻይና ከተሞች ጋር በቅርበት እየሰራች መሆኑን አንስተዋል፡፡
አዲስ አበባ ከቾንቺን ከተማ ጋር የእህትማማችነት ሥምምነት እንድትፈራረም እና ግንኙነቱ ይበልጥ እንዲጠናከር ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸውን ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
ከተሞቹ በኢኮኖሚ ትብብር፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በቴክኒክና ሞያ ፣ በነፃ የትምህርት ዕድል እንዲሁም በባሕልና ቱሪዝም ዘርፎች ላይ በጋራ ለመሥራት የእህትማማችነት ሥምምነት ለመፈራረም መዘጋጀታቸውም ተጠቁሟል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!