Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የትራኮማ በሽታን ለማጥፋት የተሠራው ሥራ ውጤታማ መሆኑ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የትራኮማ በሽታን ለማጥፋት የተሠራው ሥራ ውጤታማ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ሚኒስቴሩ የትራኮማ በሽታን ለመከላከል ብሎም ለማጥፋ ላለፉት 10 ዓመታት በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን አስታውሷል፡፡

በዛሬው ዕለትም የተመዘገቡትን ውጤቶች በሠነድ መልክ ለማስቀመጥ ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ጋር በአዲስ አባባ ባካሄደው የውይይት መድረክ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ÷ እንደ ሀገር የትራኮማ በሽታን ለመቆጣጠር በተወሰዱ እርምጃዎች የሥርጭት ምጣኔውን ከ28 በመቶ ወደ 12 በመቶ መቀነስ ተችሏል ብለዋል፡፡

በሽታው በኅብረተሰቡ ጤና ላይ ዘርፈ ብዙ ጫና ሲያደርስ እንደነበር አስታውሰው÷ ለጉዳዩ በተሰጠው ልዩ ትኩረት ኅብረተሰቡን በማሳተፍ የሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ባደረጉት ርብርብ የሥርጭት ምጣኔውን መቀነስ እንደተቻለም ገልፀዋል፡፡

በሽታውን ለኅብረተሰብ የጤና ሥጋት መሆን ወደ ማይችልበት ደረጃ ለማድረስና ጨርሶ ለማጥፋት ከሠነዱ ዝግጅት ጎን ለጎን ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ሚኒስትር ዴዔታው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በጤና ሚኒስቴር የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር መሪ ሥራ አሥፈፃሚና ትኩረት የሚሹ የሀሩራማ በሽታዎች ዴስክ አስተባባሪ አቶ ፍቅሬ ሰይፉ በበኩላቸው÷ ከ290 በላይ በሚሆኑ ወረዳዎች በሽታው መቀነሱን መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version