የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ለ225 ወገኖች ማዕድ አጋሩ

By ዮሐንስ ደርበው

January 05, 2024

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው 225 ወገኖች ማዕድ አጋርተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማዕድ ያጋሩት ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች እና ጽሕፈት ቤቱ ለሚያሳድጋቸው አሳዳጊ አልባ ሕጻናት መሆኑ ተገልጿል፡፡