አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘንድሮ ከ2 ቢልየን በላይ ቡና፣ ከግማሽ ቢልየን በላይ ፍራፍሬ እና ከ400 ሚልየን በላይ የሻይ ተክል ዝግጅት መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ እስካሁን ከነበረን በከፍተኛ ሁኔታ ተሻሽሎ በቡና፣ በፍራፍሬ እና በሻይ ላይ ያተኮር ዝግጅት እያደረግን ነው ብለዋል።
ይህንን በደንብ ተክለን ወደ ምርት ካሣደግነውም÷ በአጠቃላይ ኢኮኖሚያችን እና በዓየር ንብረት ጥበቃ ላይ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ ይሆናል ነው ያሉት በመልዕክታቸው፡፡