አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ተቋማት የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት የእውቅና አሰጣጥ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ ተካሂዷል፡፡
በመርሐ ግብሩ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ፣ የፌደራል ተቋማት አደረጃጀት ሰብሳቢ አለሙ ስሜን (ዶ/ር) ጨምሮ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
የአመራር እና የአባላት ጥራት ለማምጣት፣ የፓርቲውን ፖሊሲ እና ስትራቴጂዎች በተገቢው ሁኔታ በማስረፅ፣ አሰባሳቢ ትርክቶችን በመገንባት ረገድ በፓርቲው አደረጃጀት ውስጥ ጉልህ ተሳትፎ የነበራቸው ተቋማት እና አመራሮች ተሸላሚ ሆነዋል።
በዚሁ ወቅት አቶ አደም ፋራህ ባደረጉት ንግግር ÷ አመራሩ በዋናነት አራት ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል።
የጋራ አስተዳደር መምራት፣ የብሄራዊነት ትርክትን ማስረፅ፣ ፓርቲውን በሃሳብ ማጠናከር፣ በዲሲፕሊን አርዓያ መሆን እንዲሁም በምርጫ ማግስት ለህዝብ ቃል የገባውን ጉዳይ መፈፀም እንደሆኑ አንስተዋል።
ዓበይት ነጥቦችንም ተግባራዊ በማድረግ ከልዩነት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች መርታት፣ አስተሳሳሪ የሆኑ ትርክቶችን ለመገንባት መታተር እንደሚገባም መግለጻቸውን ከፓርቲው የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
አለሙ ስሜ (ዶ/ር) በበኩላቸው ÷ ፓርቲው ብሔራዊነትን ለማስረፅ በመትጋት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
የሚደረጉ ጥረቶችም አበረታች መሆናቸውን ጠቅሰው ÷ ጥረቶቹም መጠናከር እንደሚገባቸው አብራርተዋል።