አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ የህይወት ተሞክሮ ላይ ተመርኩዞ የተፃፈው እና “ሆኖ መገኘት” የተሰኘው መጽሐፍ በዛሬው እለት ተመርቋል።
መፅሐፉ አትሌት ሻለቃ ሐይሌ ገ/ሥላሴ እና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት ነው የተመረቀው፡፡
መፅሐፉ የአትሌቱን የሆቴሎች አገልግሎት አሰጣጥ ባህልና ተሞክሮን በድርጅት ለማስረፅ ያለመ መሆኑም ተገልጿል።
የአትሌቱን የስኬት ጉዞ እያንዳንዱ ሰው ሊኖረው የሚገባ የህይወት መርሆዎችን እና ባህርያት በተግባር የሚያሳይ በመሆኑ በመፅሐፍ መልክ ቢቀርብ በርካቶች ይማሩበታል በሚል እሳቤ እንደታተመም ተጠቅሷል፡፡
ሰዎች አንብበው ውጤታማ እንዲሆኑ፣ የድርጅት አመራር ጥበብን እንዲያሻሽሉ ለማድረግም እንደሚረዳም ነው የተጠቆመው።
አትሌት ሻለቃ ሀይሌ ገብረ ስላሴ በዚሁ ወቅት÷“በኢትዮጵያ ቢሆኑ ብዬ የምመኛቸውን ሃሳቦች ይዞ የተፃፈ በመሆኑ ደስ ብሎኛል” ብሏል፡፡
“ሆኖ መገኘት” መጽሐፍ በአቶ ፋሲል መንግስቴ እና በአቶ መልካሙ መኮንን የተዘጋጀ ሲሆን ÷ በአቶ ደሳለኝ ሥዩም ተሰናድቷልም ነው የተባለው።
መጽሐፉን አዘጋጅቶ ለንባብ ለማብቃትም ሦስት ዓመት እንደፈጀ በመርሐ ግብሩ ተገልጿል።
በቅድስት አባተ