አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ የተገነቡ 389 ቤቶችን ለዓቅመ ደካሞችና ለሀገር ባለውለታዎች አስረክበዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሉት ፥ ልበ ቀና ባለሃብቶችንና ሌሎች አቅሞቻችንን በማስተባበር በከተማችን 389 ቤቶችን ገንብተን በማጠናቀቅ ለአቅመ ደካሞችና ለሃገር ባለውለታ ነዋሪዎቻችን በማስረከብ ችግሮቻቸውን አቃለናል።
አክለውም በልብ ቀናነት ማህበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት ለሌሎች ደስታን የምትለግሱ ሁሉ፣ በጎነት አያጎድልምና በተጠቃሚዎቹ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁም ብለዋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.) ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!