Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት የወንጪ ደንዲ ሐይቅ ኢኮ ቱሪዝምን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የወንጪ ደንዲ ሐይቅ ኢኮ ቱሪዝምን ጎበኙ፡፡

በጉብኝት መርሐ-ግብሩ የሀገር መከላከያ ሚኒስትር አብርሐም በላይ (ዶ/ር)፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የኦሮሚያ ከተሞች ክላስተር አስተባባሪ አቶ መስፍን መላኩና ሌሎች እንግዶችም መገኘታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

አምባሳደር ሬድዋን በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት÷ ኢትዮጵያ ዕምቅ የተፈጥሮ ሐብት ያላት ሀገር ብትሆንም ዘርፉን ባለማልማቷ ተጠቃሚ ሳትሆን ቆይታለች፡፡

በአሁኑ ወቅት ግን መንግሥት ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት በመሥጠቱ የሀገሪቷን ገፅታ ለመለወጥ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

የተፈጥሮ ሐብቶችን በማልማት እና በማስተዋወቅ ረገድ ሠፊ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ በትናንትናው ዕለት የባሕር በር ማግኘት የሚያስችላትን ሥምምነት ከሶማሊላንድ ጋር መፈራረሟን አስታውሰው÷ በቀጣይም ትብብሩ በቱሪዝም፣ ባሕል እና በተለያዩ ዘርፎች እንደሚጠናከር አብራርተዋል።

በተጨማሪም ከጎረቤት ሀገራት ጋር የተጀመረው ጥምረት እና ሥምምነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ተናግረዋል፡፡

የሀገር ሽማግሌዎች እንግዶቹን በኦሮሞ ሕዝብ ባሕል መሠረት ደማቅ አቀባል ማድረጋቸውም ተመልክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version