Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት እየተሠራ መሆኑ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት የምግብና መጠጥ ምርቶችን ጨምሮ ጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳትን ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ለማምረት ዕቅድ መያዙን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የተኪ ምርት ስትራቴጂው ሀገራዊ ዐቅምን ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑን የዕድገትና ተወዳዳሪነት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ አስረድተዋል።

በተለይም የግብርናው ዘርፍ ዕድገት የምግብና መጠጥ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለማምረት ምቹ አጋጣሚ እንደሚፈጥርም ነው ያመላከቱት፡፡

ዕሴት የመጨመር ጉዳይ ላይም በትኩረት እንደሚሠራ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

አቶ ታረቀኝ በ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ ÷ ወታደራዊ ልብሶችና ጫማዎች እንዲሁም የተማሪ ዩኒፎርሞችን ሙሉ ለሙሉ በሀገር ውስጥ ማምረት መቻሉን አንስታውቀዋል፡፡

በያዝነው በጀት ዓመት አምሥት ወራትም 852 ነጥብ 2 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ያላቸውን ምርቶች በሀገር ውስጥ ማምረት መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡

በ2016 ዓ.ም 2 ነጥብ 315 ቢሊየን ዶላር ዋጋ ያላቸውን ምርቶች በሀገር ውስጥ በማምረት የውጭ ምንዛሬ ወጪን ለማስቀረት ታቅዷል ማለታቸውን ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የስትራቴጂው ዋና ዓላማ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት አምራች ዘርፉን ማሳደግና ተወዳዳሪነቱን መጨመር መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version