አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እና ሶማሌ ላንድ የባሕር በር ሥምምነት ጥበብ የተሞላ ዲፕሎማሲ፣ አብሮ የማደግ ብሂል እና በቅንነት የተጀመረ የዕድገት ጉዞ ሥኬት መገለጫ ነው ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሠ-መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡
ርዕሠ-መሥተዳድሩ ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን የመግባቢያ ሥምምነት ከሶማሌ ላንድ ጋር በመፈራረሟ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
አቶ ጥላሁን በማኅበራዊ ትሥሥር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን የመግባቢያ ሥምምነት መፈረሟን ጠቅሰው አመስግነዋል፡፡