አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሊዮኔል ሜሲ እግር ኳስ ካቆመ በኋላ 10 ቁጥር መለያው በሌላ ተጫዋች ሊለበስ እንደማይችል የአርጅንቲና እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡
የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ክላውዲዮ ታፒያ÷የሊዮኔል ሜሲ10 ቁጥር መለያ ለዘላለም ተከብሮለት ይኖራል፤እኛ ለእርሱ የምናደርግለት ትንሹ ነገር ይህ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ሜሲ ሀገሩ አርጀንቲና ከፈረንጆቹ 1986 በኋላ ለ3ኛ ጊዜ ባነሳችው የኳታሩ ዓለም ዋንጫ 7 ግቦችን በማስቆጠር ለቡድኑ ስኬት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱ ይታወሳል፡፡
ሀገሩ የዓለም ዋንጫን እንድታነሳ ከማድረጉ ባለፈም ሜሲ ለአርጀንቲና 108 ጨዋታዎችን አድርጎ 106 ግቦችን በማስቆጠር የአርጀንቲና የምንጊዜም ባለውለታ መሆን ችሏል፡፡
በአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር እየተጫወተ የሚገኘው ሜሲ÷ በ2026 ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ከአርጅንቲና ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ጋር ሊካተት እንደሚችል አለመረጋገጡን ስፖርት ሞል አስነብቧል፡፡